Tumim Song 6
እንደ አንተ አላየሁም




እንደ አንተ አላየሁም

Tempo= ----
Trans= +1
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>

0:00
0:00



እንደ አንተ አላየሁም የሚያግዘኝ
በጨነቀኝ ጊዜ
ባለቀ ሰዓት ላይ
እቅፍ አድርጎ ሚሸከመኝ

በመንታ መንገድ ላይ ሆኜ ሳለሁኝ
እጅግ ስፍገመገም ማምለጥ አቅቶኝ
ለእኔ ህይወት ብለህ የሞትክልኝ ጌታ
ፈጥነህ ደረስክልኝ የማታ የማታ

ሠላም አጥቼ ሁሌ ሳነባ
የሚረዳኝ ጠፍቶ ግራ ስጋባ
ለማይረባ ነገር ብዙ ስለፋ
አምላክ ደረስክልኝ የህይወቴ ተስፋ

ረዳት ከወዴት ብዬ ስጣራ
ዙሪያዬ ሁሉ ሆኖ ተራራ
ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሳለሁኝ
የልቤ ጌታ ከተፍ አልክልኝ

ለውለታህ ምላሽ ምን እከፍላለሁ
ቀንበሬን ሰብረህ ነፃ ወጥቻለሁ
የምስጋና መስዋት በፊትህ አቀርባለሁ
ተመስገን ተመስገን ዛሬም እላለሁ


ቅጥያ፡-
እጄን ይዘህ አንተ ስትመራኝ
እሄዳለሁ X2 ሀገሬ በሰማይ ነው
ዋአ ኢኮቶ ኢና

View Favorites