Tumim Song 1
‎እግዚአብሄርን ለሚወዱት




‎እግዚአብሄርን ለሚወዱት

Tempo= -94
Trans= -4
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>

0:00
0:00



‎እግዚአብሄርን ለሚወዱት
‎እንደ ሀሳቡም ለተጠሩት
‎ሁሉ ለበጎ ነው (X2)
‎ቃሉ እንደሚለው

‎በእርሱ የሚተማመኑ ሀይላቸውን ያድሳሉ
‎እንደ ንስር በከፍታዎች ላይ ይሄዳሉ
‎በርሀብ ዘመን ይጠግባሉ በችግር ጊዜ ይፅናናሉ
‎ሀይላቸው በሆነው በጌታ በፀጋ ይኖራሉ

‎መገፋት መሰደድ መራብም መጠማት
‎ሁሉም ቢደራረብ ማግኘትና ማጣት
‎እንደ እግ/ር ቃል ሁሉ ለበጎ ነው
‎የማታ የማታ ድሉ የጌታ ነው

‎አይጥልም እግ/ር የተደገፉትን
‎በህይወት ያኖራቸዋል መመኪያ ያደረጉትን
‎ጌታ መታመኛቸው የሆነላቸው
‎ዘመናቸው በከንቱ አያልቅባቸው

View Favorites