Ballad Song 18
የታለ ያትውልድ




የታለ ያትውልድ

Tempo= 80
Trans= -4
Style= 6-8Soul
Scale= Tizita Major
Cord= C Major
>>>>>>

0:00
0:00



የታለ ያትውልድ አምላኩን ፈላጊ
ለሐጢያት ያልተገዛ የፅድቅ ፋና ወጊ
እግዚአብሔርን መምሰል ያደረገ ግቡ
የዚ አለም ምስል የሌለ በልቡ

የጌታ እንዳይሉን አለም አለ በኛ
የአለም እንዳይሉን የቤቱ ዋነኛ
ዘመን አመጣሹን ዘመን ይመልሰው
ዘመኑ ዘምኖ እሮጦ ማለፍ ነው
ጆሮ ዳባ ልበስ ብንለውም ጌታን
ድምፁን ያስተጋባል ተነሽ ተለይ ይላል {x2}

ተነስ ወንድሜ ተነስ
ተነሽ እሕቴ ተነሽ
ተነስ ትውልዱ ተነስ
ተነስ የዕቃ ጦር ልበስ

የመኖር ትርጉሙ አላማው ተፍቶብን
ከምንጩ ተተክለን ፍሬ ቢስ ሆነን
የልጁን መልክ ትተን ሌላውን ስንመስል
ላለመኖር ምክንያት ብዙ ስንደረድር

ሙሽራው መጥቶብን
ዘይታችን አልቆ
እንዳንቀር ጨልመን
ጭላንጭሉም ጠፍቶ

ምስጉን ነው{3×}
የአምላኩን ፊት የሚፈልገው

View Favorites