Tempo= 63
Trans= +1
Style= HB Balled
Scale= Tizita Major
Cord= Am
>>>>>>
የነፍስን ፍላጎት ረሀብ የሚያጠግብ
መዋተቷን ገቶ ሰላም የሚያሰፍን
አስከፊው ጥሟን በፍቅሩ የሚያርስ
እውነተኛ ዳኛ ያለው ከጌታ ዘንድ ነው
አገኘች እውነተኛ እርካታ
አገኘች ነፍሴ
አገኘች ሰላሟ ፀናላት
አገኘች ጌታዋን
ልኬት የሌለው የክብርህ ብልፅግና
የሚስብ ማንነት ከፍ ያለ ግርማህ
ግብዝነት የሌለው ባህሪህ ውብ ነው
ምን መተኪያ አለው ህልውና
ሕልውናህ {6×}
መገኘትህ {6×}
እጅግ መልካም ነው መኖር በኃልዎትህ
አንተ ባለህበት የሚስብ መአዛ
ነፍሴ አርፋለች ከመቅበዝበዝ ሩጫ
በሕልውናህ ውስጥ አግኝታለች ብልጫ
ረሀቤ ነህ
ናፍቆቴ ነህ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ከአንተ ወደ ማን