Ballad Song 11
ሕይወቴ ያክብርህ




ሕይወቴ ያክብርህ

Tempo= __
Trans= __
Style= Lovesong
Scale= Tizita Major
Cord= C Major
>>>>>>

0:00
0:00



ሕይወቴ ያክብርህ ነፍሴ ትቀኝልህ
ልኑርልህ ጌታ ልኑርልህ {2x}

እርሱ ስለ እኛ ሞተ እኛም ከርሱ ጋር በሕብረት
የምድር ኑሮአችን ሁሉ ሊሆን ለእርሱ መስእዋት
ስለኛ ለሞተው እንጂ ከእንግዲህ እንዳንኖር ለእኛ
በሞቱ አፅንቶታል የኑሮአችን ግቡ እንዲሆን ለራሱ

እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው ጥማታችን
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው መሻታችን

ከአንተ ጋር ተሰቅለን ከእንግዲህ እኛ እንዳንኖር
ያበዛልንን ፀጋ እንደ ስንቱ እንደ ቃል
የስጋ ምኞታችንን በሙሉ እየገደልን
መኖር ለሚገባን በሙላት ለአንተ እንድንኖር

እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው ጥማታችን
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው መሻታችን

ከቃላት ይለፍ ኑሮ
ከመዝሙር ይለፍ ኑሮ
ያክብርህ ሕይወታችን

View Favorites