Tempo= 81
Trans= +5
Style= ___
Scale= Tizita Major
Cord= ___
>>>>>>
ኤልያቄም
እግዚአብሔር ትውልድ ያስነሳል
ባለፈው ትውልድ ጌታ ካዘን
የልቡን የሚመልስ ካላገኘ
አሁን ከዙፋኑ ይነሳል
በቅዱስ መንፈሱ ይገባና
ለፈቃዱ ያሰማራል ጌታ
የእምነት አባቶች እንባ አሀ
የቤተ ክርስቲያን ጬኸት
እንዲሁ አልቀረም አልወደቀም
ጌታ በልጆቹ አልጨከነም
በነ ኤልያስ ዘመን በነ ጳውሎስ
እርሱ ለትውልድ በነሱ ሲደርስ
አሁን ላለው ደግሞ መቼ ጨከነ
ጌታ ለልጆቹ እጅጉን አዘነ
ትውልድ ሊያስነሳ ወሰነ
ቃል ነበር ጅማሬው አምላክ ከጥንት የገባው
አብሮት ሊሰራ ያየ ትውልድ አለው
በዘመን መሀከል እንደ ጊዜው ሚተካው
አብሮት የሚያብር ሰራዊት አለው
ኤልያቄም {2×} እግዚአብሔር ያስነሳል
ኤልያቄም {2×} በዘመናት ላይ
ኤልያቄም {2x} ለሀሳቡ ሚልከው
ኤልያቄም {2×} መልዕክተኛ አለው