Tempo= ___
Trans= ___
Style= Walze
Scale= Tizita Major
Cord= Am
>>>>>>
ቤተክርስቲያን ልጆች ብዙ እንዲወለዱ
ግድ ይለሻል ብዙ ማልቀሱ {ማማጡ}
ለምን ምጥ በመሀል
ለምን ታቋርጫለሽ
ለምን ጭንቀቱን ፈርተሽ
ለምን በልጆችሽ ጨቀንሽ
በጭንቅ በምጥ የሚወለዱ ካንቺ
አልጠፋምና ከጉያሽ
በጭንቅ በምጥ የሚወለዱ ካንቺ
አልጠፋምና ከጉያሽ
ሲያዬ ቢበዛም ወልደሽ ተገላገይ
አጋዥ አለሽና ከሰማይ ረዳት አለሽና ከላይ
ዉለጂው ነውና መልካም
ዉለጂው ቢበዛም ድካም
ዉለጂው ታርፊያለሽና
ዉለጂው ትውልድ ያድናሉና
ፈቃዱን የሚሰም የሚያደርግ
የሚከተል የእየሱስን ፈለግ
ትውልድን የሚመልስ የሚያድን
ነውና ቀጥይ ምጡን
ትውልድ እንዲያርፍ
ትውልድ ግራ እንዳይገባው
ትውልድ እንዲያመልጥ
ያስፈልጋል የአንቺ ትጋት