Tempo= 117
Trans= +3
Style= ChichChika
Scale= Tizita major
Cord= C
>>>>>>
ገዚ የተባልከው
አባት የተባልከው
አምላክ የተባልከው
ትልቅ የተባልከው
መች በታሪክ ሆነና እንደ ተረት
አይናችን አይቶታል ይህን ትልቅነት
ክበር እንኩኣን ባንል ከፍ ዝቅ የማትል
ፀንተ የምትኖር አንተ አምላካችን
ክበር ክበር ክበር እንላለን
ታላቅነትህን ክብርህን እያየን
ክበር ክበር ክበር እንላለን
ታላቅነትህን ግርማህን እያየን
ስለ ትልቅነትህ ፍጥረት ይናገራሉ
ያንተን ገናናነት ሁሌ ያወራሉ
ተፈርተህ የምትኖር በሰማይ የምትኖር
ግሩም አምላካችን አንተ ነህ እግ/ር
ሰዎች ሲደመሩ ሀያል ነን ለማለት
ክብር ዝናቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ
መቼ ከብረው ኖሩ አይተናቸዋል
አለ በዙፋንህ ጥንት እንደነበርከው
ክበር ክበር ክበር እንላለን
ታላቅነትህን ክብርህን እያየን
ክበር ክበር ክበር እንላለን
ታላቅነትህን ግርማህን እያየን