Tempo= 120
Trans= 0
Style= ChickChika
Scale= Anchoyelene
Cord= Bm
>>>>>>
ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ያለህ
ፍጥረታትን በሙሉ በስልጣን ታዛለህ
ይሁን ብቻ በሚለው ቃል ሁሉ የሆነልህ
የሰውንም ልጅ በኃምሳል ለክብርህ ፈጠርህ
ሰማያት ክብርህን ይናገራሉ
የሰማይ ጠፋር ስራህን ስራህን ያወራሉ
ቀንም ለቀን ሌትም ለሌት እዉቀትን ይገልጣል
ድምፃቸው እስከ ምድር ዳርቻ ይወጣል
እግዚአብሔር {4×} ክቡር ነህ {4×}
እውቀትህ ረቂቅ
ስራህ ሁሌም ድንቅ
ባማረ መዝሙር
ፍጥረት ይበልህ ክቡር
ክቡር ነህ {4×}
ድንቅ ነህ {4×} ሚመስልህ የለህ
የንጋት ከዋክብት በዘመሩ ጊዜ
መላእክት በአንድነት እልል ባሉ ጊዜ
የምድር መሰረት ማዕዘንኣ ቆመ
ይሁን ያልከው ሁሉ ቃልህን ታዘዘ
ከአማልክት መኃል እጅግ ባለግርማህ
ቅዱስነትህ ለፍጥረት ይሰማ
ዘመንህ የሌለው መነሻ መድረሻ
ዘለአለም ነዋሪ ጌታ አንተ ብቻ
የሽሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ
በደመናት ላይ ለታለቅነትህ {2×}
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለ {2x}