Tempo= 95
Trans= +3
Style= -- Wallo
Scale= Tizita Major
Cord= C Major
>>>>>>
እንዴት ያለ ምንጭ ነው የፈለቀልኝ
የዘላለም ጥሜንም የቆረጠልኝ
ከእየሱስ ሚፈልቀዉ የዘላለም ሕይወት
ደረቁን ሚያለመልም እንከን የሌለበት
አቤት እንዴት እንዴት ግሩም ነው
ለተጠማው የሕይወት ምንጭ ነው {x2}
ተነሺ ማለዳ ነፍሴን ለማመስገን
እንዴት ያስችልሻል የረገልሽ ነገር
ከጨለማ አውጥቶ ብርሀን ያበራልሽ
ቀንበርሽን ሰብሮ ነፃ ያወጣሽ
ተሽሮልሽ የሞት አዋጅ በእርሱ
ታወጀልሽ አርነት በእየሱስ
እርሱን የተከተለ ከልቡ ተማምኖ
ፍፃሜውም አማረ በጥላው ስር ሆኖ
በሆነለት ቤዛነት በእርሱ ያረፈ
ከሀጥያት ጥፋት ባርነት እርሱ አመለጠ
በቀራኒዮ ላይ ተሰቅሎ
ለሰው ልጆች ሁሉ ዋጋ አከፍሎ
ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና
መቃብር ፈንቅሎ ተነቷል ጌታ
አቤት እንዴት እንዴት ታደለ
በማዳን ሀይሉ በርሱ ያመነ {x2}
ይፈልቃል ምስጋና ሁሌ ከአንደበቴ
በአሰላሰልኩ ጊዜ መዳኔን በአባቴ
ቅኔን እቀኛለሁ ለስሙ ምስጋና
ባወድሰው አልቀር ጠዋትና ማታ
ተመስገንልኝ ከፍ በልልኝ
መዳኔ በአንተ ተፈፀመልኝ {x2}