Tempo= ___
Trans= ___
Style= Slow Rock
Scale= Tizita Major
Cord= ___
>>>>>>
እየሱስ ክርስቶስ የአለም መድኃኒት
ለሰው ልጅ መዳን ተጋ ቀን ከለሊት
መስቀል ተሸክሞ በጎልጎታ ሞቶ
እኔን አንተን አንቺን ነፃ ሊያደርግ ወዶ {x2}
አዳነን {x3} ራሱን ሰዋልን
አዳነን {x3} ቤዛ ሆነልን
ከሰማያት ወርዶ እራሱን አዋርዶ
ያለ ኃጢያት ሀጢያተኛ ሆኖ
ፍቅር አስገድዶት ታላቁን መከራ
ተወጣ ፃድቁ ሞታችንን ከክፉ
አዳነን {x3} ራሱን ሰዋልን
አዳነን {x3} ቤዛ ሆነልን
ከሰማይ ሰማያት ስለኛ ወረደ
የሰው ልጅን ሀጢያት በደሙ አስወገደ
መራራውን ፅቃ እርሱ ጠጥቶታል
በእየሱስ ቤዛነት መዳን ሆኖልናል
ወረደ ወረደ ንጉስ ተዋረደ
ያለ ሀጢያቱ ለኛ ሲል ወረደ
እኛ እንድንኖር እርሱ ሞቶልናል
የእግዚአብሄር ልጅ እየሱስ ነፃ አውጥቶናል