1.

EP Balled
2.

HB Ballad
3.

Blues 6-8
4.

Walze
5.

Lovesong
6.

Lovesong
7.

Love Song
8.

-----
9.

Walze
10.

-----
11.

-----
12.

Lovesong
13.

Lovesong
14.

Lovesong
15.

HB Ballad
16.

Lovesong
17.

HB Ballad
18.

Love song
19.

Bluse 6-8
20.

Root Bluse
21.

-----
1.

Happy Reggae
2.

Reggae
3.

Reggae
1.

Hard Rock
2.

Root Rock
3.

Pop Shuffle
4.

Charlston
5.

Charlston
6.

ChickChika
7.

-----
8.

Hard Rock
9.

Hard Rock
1.

6-8 soul
2.

Hab wereb
3.

Slow Rock
4.

Wallo
5.

Slow Rock
6.

Chickchika
7.

Wallo
የደም ዋጋ የተከፈለ
በመስቀል ለይ ተንከራቶልኝ
ለኔ ራርቶ የተቀጣልኝ
ራሱን ሰቶ ፍቅሩን ገለጠልኝ {x2}
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነው {x2}
ለኔም ለወንድሜም ለእህቴም
ጻድቅ ሆነ ሳለ የሞትክልን
ባጢያታችን ከመገረፍ ያዳንከን ጌታ
ላንተ ይገባሃል ምስጋና {x3}
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነው {x2}
እንደሚታረድ በግ የተነዳው
ጻድቅ ሆኖ ሳለ ኃጢያት የሆነው
ለኔ ነው ለኔ ነው
እንደሚታረድ በግ የተነዳው
ራሱን ሰቶ በመስቀል የሞተው
ለኔ ነው ለኔ ነው
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነው {x2}
ምስጋና ምስጋና
ምስጋና ብዙ አለን ተደርጎልናልና {x2}
በመልካሙ አጅ ተጎብኝተናል {x2}
ሀዘናችን ርቆ ሀሴት ተሞልተናል {x2}
ከበረከትህና ከጠል ረስርሰናል
ሃሌሉያ ክበር በአንተ አርፈናል {x2}
ምስጋና ምስጋና
ምስጋና ብዙ አለን ተደርጎልናልና {x2}
ሃይል ለማዳን ሆኖ እንዳንጠፋ ተጠብቀን {x2}
እግሮቻችን ጸኑ አረማመዳችንም ቀና {x2}
አቤነዘር ትላንት እስከ ዛሬ ረድተህናል
ለነገም አልፈራም ባንተ ተጠብቀናል {x2}
ምስጋና ምስጋና
ምስጋና ብዙ አለን ተደርጎልናልና {x2}
አቤቱ እንዴት ታላቅ ነህ
አቤቱ እንዴት ግሩም ነህ {x2}
የሰማይ ፍጥረት የሆኑት መልዕክት
ከዘላለም በፊት ሲሉ ቅዱስ ቅዱስ
ዛሬ ሰልችቶአቸው አምልኮ አላቆሙም
በዘላለሙ ሕዝብ አንተ አትለመድም
አትለመኸድም
አትቀየኸርም
ክብርህ አያረጅም
ዘመንህ አያልቅም
ውበትህ አይረግፍም
ውበት ግርማህ ጥበብ ችሎታህ
እውቀት ምጥቀትህ ቅድስናህ
ማርኮናል {x3} እኛ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ
ፊትህ እንደ ፀሐይ ያበራል
ዓይኖችህ የእሳት ነበልባል ናቸው
ድምፅህ እንደ ብዙ ውሆች ድምፅ ነው
ስምህ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ነው
የዘላለም አምላክ አማኑኤል
ምስጋና ይፈልቃል ከአንደበቴ
ምህረትህ ገኗል በህይወቴ
ማዳንህን እናገራለው
ቸርነትህን በአይኔ አይቻለው
ትናንትን ያለፍኩብህ
ዛሬንም ያየሁብህ
ለነገም ተስፋዬ ነህ
ኢየሱስ ነፍሴ አመነችህ
ማኖሬ ትርጉም አገኘ በአንቴ አምለኬ
እንድኖር ተመኝው እንደገና ስለሌ ከኔ ጋር
ከቶ አለስብም ወደ እስር ልመለስ
ነፍሴ ወደሃሌች ለዘላለም ክበር
ከምንም የምትበልጥብኝ
ማለምድህ የመትሰለቸኝ
የቅርቤ ስለሆንክ አባቴ
እኳረሌው ስለሌህ ቤቴ
ከዙፋንህ ስር ሆነን ልናጤንልህ
የተመረጠውን መልካሙን መዓዛ
መቅደስህን ልንሞላው በአምልኮ ሽታ
ልናደናንቅህ በምስጋና
ቅዱስነት ማርኮናልና
በአንተ ዘንድ ያለው የክብርህ መዓዛ
ቅዱስ {x3} እግዚአብሔር
ሀያል {x3} እግዚአብሔር
ክቡር {x3} እግዚአብሔር
ታላቅ {x3} እግዚአብሔር
ሳበንና አቅርበንና
የክብር ፀዳል ያብራልንና
የተጋረደውን የስርዓት ግርዶሽ
ተቀዶ ይነሳ ለእውነት አምልኮ
እናመልክሀለን {x3} ጌታ
እናከብርሀለን {x3} ጌታ
ቅዱስ ነህ ፃዲቅ ነህ ሀያል ነህ እያልን
አምላካችን ኃይላችን
ባገኘን በታላቅ መከራ ረዳታችን
ስለዚህ ምድር ብትናወጥ
ተራሮች ወደ ባህር ቢጣሉ
ከኛ ጋር ነህ አንፈራም
እረኛችን{×4}
መልካም አምላክ የልጆች እረኛ
ትጠብቀናለህ ላፍታ አተኛ
ነፍሳችንን ከሚሹት ትጠብቀናለህ
ከቀን ፍላፃ በጉያህ ትሸሽገናለህ
የኛ ጌታ እረኛችን ነህ
የኛ እየሱስ እረኛችን ነህ
ከነገድ ከቓንቓ ከህዝብ ዋጀኸን
ያንተን መልካምነት በጎነት እንድንናገር
እኛም የምህረት ልጆችህ
መጣን ልናመልክህ
ተመስገን ልንልህ
ተባረክ ልንልህ
ከፍ በል ልንልህ
ኦሆ ልናመልክህ
ባለን መልካምነት ሳይሆን
በበዛው ምህረት
በፊትህ ፀድቀናል ኩነኔ የለብንም
ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው
አሮጌው አልፎአል ፀጋህን ለበብሰናል
በፊት በጨለማ ነበርን ተስፋ በሌለበት
ህይወት {x3} ቀርቶ ምት ምት ሚሸትበት
ግን በቀራንዮ ላይ በከፈለው ዋጋ
ወደ ሚደነቅው ብርሃን መጥተናል በፀጋው
ፀጋህ ሰው አረገኝ
ምረትህ ሰው አረገኝ
ይቅርታህ ሰው አረገኝ
ኦሆ አረገን ሰው አረገኝ
አትሸበሩ ፀንታችሁ ቁሙ
ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃዊያንን
ዳግም አታዩአቸውምና
እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙም እግዚአብሔር ነው
የፈርኦንን ሰረገሎች ባህር ውስጥ ጠላቸው
ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባህር ጥሎአልና
ክብር ለእግዚአብሔር ለሆነው ገናና
ፈርኦን ከኃላዬ ቢገሰግስም
ሊይዘኝ ሳይሆን ነው ለመስጠም
ተስፋ ቢያስቆርጠኝ የጊዜው ሁኔታ
እግዚአብሔር አይጥልም ከቶ ለአንድ አፍታ
ክፍተት ፈልጎ በሕይወቴ ቀዳዳ
ለጥፋት ጥፍሮቹን ሲያሳየኝ
መቼ አባቴ ይተኛል ስለእኔ
አሁንም ህያው ነው ኪዳኔ
እግዚአብሔር ይመራል ልጆቹን በድንቅ
ቀን ላይ በደመና ሌሊት በእሳት አምድ
እየመራኝ ወስዶ ወደ ተስፋ መንገድ
ልቤ አይደነግጥ ከቶ አልወላገድ
ቤተክርስቲያን ልጆች ብዙ እንዲወለዱ
ግድ ይለሻል ብዙ ማልቀሱ {ማማጡ}
ለምን ምጥ በመሀል
ለምን ታቋርጫለሽ
ለምን ጭንቀቱን ፈርተሽ
ለምን በልጆችሽ ጨቀንሽ
በጭንቅ በምጥ የሚወለዱ ካንቺ
አልጠፋምና ከጉያሽ
በጭንቅ በምጥ የሚወለዱ ካንቺ
አልጠፋምና ከጉያሽ
ሲያዬ ቢበዛም ወልደሽ ተገላገይ
አጋዥ አለሽና ከሰማይ ረዳት አለሽና ከላይ
ዉለጂው ነውና መልካም
ዉለጂው ቢበዛም ድካም
ዉለጂው ታርፊያለሽና
ዉለጂው ትውልድ ያድናሉና
ፈቃዱን የሚሰም የሚያደርግ
የሚከተል የእየሱስን ፈለግ
ትውልድን የሚመልስ የሚያድን
ነውና ቀጥይ ምጡን
ትውልድ እንዲያርፍ
ትውልድ ግራ እንዳይገባው
ትውልድ እንዲያመልጥ
ያስፈልጋል የአንቺ ትጋት
ኤልያቄም
እግዚአብሔር ትውልድ ያስነሳል
ባለፈው ትውልድ ጌታ ካዘን
የልቡን የሚመልስ ካላገኘ
አሁን ከዙፋኑ ይነሳል
በቅዱስ መንፈሱ ይገባና
ለፈቃዱ ያሰማራል ጌታ
የእምነት አባቶች እንባ አሀ
የቤተ ክርስቲያን ጬኸት
እንዲሁ አልቀረም አልወደቀም
ጌታ በልጆቹ አልጨከነም
በነ ኤልያስ ዘመን በነ ጳውሎስ
እርሱ ለትውልድ በነሱ ሲደርስ
አሁን ላለው ደግሞ መቼ ጨከነ
ጌታ ለልጆቹ እጅጉን አዘነ
ትውልድ ሊያስነሳ ወሰነ
ቃል ነበር ጅማሬው አምላክ ከጥንት የገባው
አብሮት ሊሰራ ያየ ትውልድ አለው
በዘመን መሀከል እንደ ጊዜው ሚተካው
አብሮት የሚያብር ሰራዊት አለው
ኤልያቄም {2×} እግዚአብሔር ያስነሳል
ኤልያቄም {2×} በዘመናት ላይ
ኤልያቄም {2x} ለሀሳቡ ሚልከው
ኤልያቄም {2×} መልዕክተኛ አለው
አቤት እየሱስ ምህረትህ
አቤት እየሱስ ፍቅርህ
ዘላለም ህያው አይበርድም
ዘላለም ህያው አያልቅም
ጎህ ሲቀድ ማለዳ ነው ምሕረቱ አዲስ
ሕይወት አገኛለሁ ብዬ እደፋለው ፊቱ
አቤት የኔ ጌታ ማለዳ ምሕረቱ
ተስፋዬንም አድሶ አቁሞኛል በቤቱ
ከፊትህ ያልጠፋነው በብዙ ምሕረትህ
ከሕይወት የሚሻለው አግኝቶናል እጅህ
በደምህ አፅንተ ፀጋን ሞልተኸናል
በዝለት እንዳንወድቅ ሐይልህ በዝቶልናል
ሕይወቴ ያክብርህ ነፍሴ ትቀኝልህ
ልኑርልህ ጌታ ልኑርልህ {2x}
እርሱ ስለ እኛ ሞተ እኛም ከርሱ ጋር በሕብረት
የምድር ኑሮአችን ሁሉ ሊሆን ለእርሱ መስእዋት
ስለኛ ለሞተው እንጂ ከእንግዲህ እንዳንኖር ለእኛ
በሞቱ አፅንቶታል የኑሮአችን ግቡ እንዲሆን ለራሱ
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው ጥማታችን
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው መሻታችን
ከአንተ ጋር ተሰቅለን ከእንግዲህ እኛ እንዳንኖር
ያበዛልንን ፀጋ እንደ ስንቱ እንደ ቃል
የስጋ ምኞታችንን በሙሉ እየገደልን
መኖር ለሚገባን በሙላት ለአንተ እንድንኖር
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው ጥማታችን
እግዚአብሔር አምላካችን ይህ ነው መሻታችን
ከቃላት ይለፍ ኑሮ
ከመዝሙር ይለፍ ኑሮ
ያክብርህ ሕይወታችን
ክብር የሚገባህ አምላክ
አምልኮና ስግደት
አንተ አይደለህም ወይ ጌታ
የሞትከው ለኔ በጎልጎታ
አንተ አይደለህም ወይ እየሱስ
የሕይወቴ ንጉስ
ለኔም ለወንድሜም ለእህቴም
ፃዲቅ ሆነ ሳለህ የሞትክልን
ከሐጢያታችን በመገረፍ ያዳንከን ጌታ
ለአንተ ይገባሀል ምስጋና {ክብር}
ክብር ሀሌሉያ
ስግደት ለመንፈስ ቅዱስ
አምልኮ ለንጉሱ
ይገባዋልና እናምልከው
ከሰማይ በታች ከምድርም በላይ
ያሉትን ፍጥረታት በሙሉ ብናይ
አንዳቸውም አልፀኑም በኃይል ብርታታቸው
በቃልህ አፀናን ሕይወት ሰጠሀቸው
ድንቅ ነህ
አለማትን በቃልህ የሰራህ
በእውነት አንተ ድንቅ ነህ
ለአፈር እስትንፋስን ሰጠኸው
ይገርማል ተባልኩኝ ሕይወት ያለው
አፋር ላይ ቆሜ ከአፈር ስሰራ
ድንቅ ነህ አልኩኝ እኔም በተራ
ድንቅ ነህ
አለማትን በቃልህ የሰራህ
በእውነት አንተ ድንቅ ነህ
እኛ ልጆችህ ተሰብስበን
እናደንቃለን በአንድነት ሆነን
ተአምራቶችህን የአንተን ስራ
እንዘምራለን ትልቅ ነህና {2×}
በእውነት እኛም አናውቅህም
ከዘለአለም ዘመናት በፊት የነበርህ
ከፍጥረት በፊት ብቻህን የኖርህ
እግዚአብሔርነትህ ልዕልህናህ
ሁሉን ቻይነትህ ልዩ
እግዚአብሔር ትልቅ ትልቅ ነህ
ፍጥረት በአንድነት አንተን ያክብርህ
የደህንነቴን ስራ አንተ ሁሉን ሰርተህ
ክብርህን ልትገልጥበት ደካማውን መርጠህ
እኔ ከእኔ ነው ምለው ምን መልካም ስራ አለኝ
ሁሉ አከአንተ ከአምላኬ ለእኔ የሆነልኝ
ክብር ለአብ
ክብር ለወልድ
ክብር ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን አሜን
ሀሌሉያ{3×} ክብር ይሁን አሜን!
በዘለአለም መንፈስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን
የራሱን ደም ይዞ አንዴ የገባልን
ተስፋ የተሰጠውን የዘለአለም ርእስት
ለእኛ ሊያወርሰን ደሙን ከፈለልኝ
ለታረደው በግ ኃይል{2×} ባለጠግነትህ
ጥበብ ብርታት ክብር{2×} ሞገስ ይሁንልህ
በሰማይ በምድር ከፍጥረተ ፍጥረት
ማተሙን ለመፍታት መፅሐፉን ለመክፈት
አንዳቸውም አልቻሉም ማንም አልተገባው
የአይሁድ አንበሳ ግን ይህን አደረገው
መፅሐፉን ትወስድ ዘንድ
ማሕተሙን ትፈታ ዘንድ
ይገባሀል
ታርደሀልና ዋጅተኸናልና
ክብር{3×} ይሁንልህ
ሀሌሉያ
የነፍስን ፍላጎት ረሀብ የሚያጠግብ
መዋተቷን ገቶ ሰላም የሚያሰፍን
አስከፊው ጥሟን በፍቅሩ የሚያርስ
እውነተኛ ዳኛ ያለው ከጌታ ዘንድ ነው
አገኘች እውነተኛ እርካታ
አገኘች ነፍሴ
አገኘች ሰላሟ ፀናላት
አገኘች ጌታዋን
ልኬት የሌለው የክብርህ ብልፅግና
የሚስብ ማንነት ከፍ ያለ ግርማህ
ግብዝነት የሌለው ባህሪህ ውብ ነው
ምን መተኪያ አለው ህልውና
ሕልውናህ {6×}
መገኘትህ {6×}
እጅግ መልካም ነው መኖር በኃልዎትህ
አንተ ባለህበት የሚስብ መአዛ
ነፍሴ አርፋለች ከመቅበዝበዝ ሩጫ
በሕልውናህ ውስጥ አግኝታለች ብልጫ
ረሀቤ ነህ
ናፍቆቴ ነህ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ከአንተ ወደ ማን
ብርቱ መሳይ ደካማነኝ
ፊትህ መጣው ተመልከተኝ
ብዙ ነው ድካሜ ይታይሃል ላንተ
ሸክም ይውለድልኝ ማረኝ መድሃኒቴ
ባዶነው ቤቴ ያለ ህልውናህ
ካልገባንበት አያምርምና
መንፈስህ ለኔ ውበት ሞገሴ
ውበቴ ደም ግባቴ
ሃይሌ ነህ ድፍረቴ
መንፈስ ቅዱስ ሙሉነቴ {x2}
ከመንፈስ በቀር የለኝ
በድፍረት ፊትህ የሚያቆመኝ
ከኔ ምለው የምቆጥረው
አንዳች የለኝ ሁሉ ካንተ ነው
ባዶነው ቤቴ ያለ ህልውናህ
ካልገባንበት አያምርምና
መንፈስህ ለኔ ውበት ሞገሴ
የህይወት መንፈስ ነህ
ወደ እውነት መሪ
ከስላሴ አንዱ አካል ዘላለም ነዋሪ
ራሴን ፈቀድኩልህ ለክብርህ እንድሆን
ገንዘብ አድርገው ይሄው ማንነቴ {x2}
የታለ ያትውልድ አምላኩን ፈላጊ
ለሐጢያት ያልተገዛ የፅድቅ ፋና ወጊ
እግዚአብሔርን መምሰል ያደረገ ግቡ
የዚ አለም ምስል የሌለ በልቡ
የጌታ እንዳይሉን አለም አለ በኛ
የአለም እንዳይሉን የቤቱ ዋነኛ
ዘመን አመጣሹን ዘመን ይመልሰው
ዘመኑ ዘምኖ እሮጦ ማለፍ ነው
ጆሮ ዳባ ልበስ ብንለውም ጌታን
ድምፁን ያስተጋባል ተነሽ ተለይ ይላል {x2}
ተነስ ወንድሜ ተነስ
ተነሽ እሕቴ ተነሽ
ተነስ ትውልዱ ተነስ
ተነስ የዕቃ ጦር ልበስ
የመኖር ትርጉሙ አላማው ተፍቶብን
ከምንጩ ተተክለን ፍሬ ቢስ ሆነን
የልጁን መልክ ትተን ሌላውን ስንመስል
ላለመኖር ምክንያት ብዙ ስንደረድር
ሙሽራው መጥቶብን ዘይታችን አልቆ
እንዳንቀር ጨልመን ጭላንጭሉም ጠፍቶ
ምስጉን ነው{3×}
የአምላኩን ፊት የሚፈልገው
የዘላለም አምላክ የዘመናት ንጉስ
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
የሚመስል የለም በሰማይ በምድር
እውነቱ በርቶልኝ ነው የአንተ ታላቅነት
ከልቤ የማመልክህ ነፍሴ ደስያላትህ
የማልፀፀትበት ሕይወት ነው የምኖረው
በአንተ ደስ እያለኝ ክብርህን እያየው
ግርማህን እያየው
በተቀደሰው ስፍራህ እሰግድልሀለሁ
በልቤ ዙፋን ላይ ውዴ ሾሜሐለሁ
ይኸው መርምረኝ ከአንተ ሌላ አላውቅም
የእስትንፋሴ ጌታ አንተ ብቻ ነህ
አንተ ብቻ ነህ
ክብርህን ተጠማን
ክብርህን ናፈቅን
ክብርህን ተጠማን
ክብርህን ናፈቅን
አረስርሰን{4×}
ተወለደ መድሀኒት ለሁሉ
ቤዛ ለአለም
ኸሀ {x2} ተወለደ ቤዛ ለአለም
ኸሀ {x2} ተወለደ ቤዛ ለአለም
ለሚጠፋት መዳን ሆነ {x3}
ምህረቱ ለሰው ልጆች ገነነ
አማኑኤል ተወለደ
በጨለማ ለነበርን ብርሃን መጣልን
እ/ግር አምላክ ከላይ ራራልን
አማኑኤል ተወለደልን
በባርነት ለነበርን እየሱስ መጣልን
ከድንግል ማርያም ተወለደ
አማኑኤል ተወለደልን
ስምህ ከስሞች ሁሉ በላይ ነው
የሰላም አለቃ የዘላለም አባት
ድንቅ መካር ነው
መዳን በሌላ በማንም የለም
እንድንድንበት የተገባ
ከሰማይ በታች አንድ ስም ብቻ
ወደር የሌለው አቻ
ያድናል ይታደጋል
ስሙን ጠርቶ ማን አፍሮ ያውቃል
የመዳን ቀንዴ ነው
የማምለጫ አለቴ
ሕይወት ማግኛዬ ነው ስምህ
የፀና ግንብ ነው የደካሞች ብርታት
የሚፈስ ከስምህ የዘላለም ሕይወት
እንደሚፈስ ዘይት ነው {3×} ስምህ
አንድ አለ በሰማይ አንድ አለ በምድር
ለሁሉም አዳኝ ሚሆን ስም
ሁል ጊዜ ካፌ ልለየው ማልችል
የነፍሴ ደስታ ፍስሀ ክብር
ኦ ስምህ ነው
ኦ ደስታዬ {2×}
እየሱስ {3×} ስምህ ልዮ ነው
እግ/ር የኔ አምላክ
ፍቅርህን ልትገልጥ ልጅህን ላክልን
እየሱሴ የኔ አባት
መጣህልን ከኃጢያት ለማውጣት
አዳንከኝ በመስቀልህ ስራ
ማርከኝ በምህረትህ
ሰጠኸኝ የዘላለም ህይወት
አለው ዛሬም በቤትህ
የመውደድህ ልክ ከቃላት በላይ ነው
እኔን ለማዳን ዋጋ የከፈልከው
ፍቅርህ ገብቶኛል አንተን ላምልክህ
በቀረው ዘመኔ ዛሬም ልገዛልህ
አዳንከኝ በመስቀልህ ስራ
ማርከኝ በምህረትህ
ሰጠኸኝ የዘላለም ህይወት
አለው ዛሬም በቤትህ
ስትወርድ ከሰማይ ከከበርክበት
ስትወደኝ እኔን ምንም በሌለበት
የፍቅርህ ብዛት ለኔ ልዩ ነው
እንዳንተ ሚሆን አንድም አላገኘው
አዳንከኝ በመስቀልህ ስራ
ማርከኝ በምህረትህ
ሰጠኸኝ የዘላለም ህይወት
አለው ዛሬም በቤትህ
አቤት እየሱስ ምህረትህ
አቤት እየሱስ ፍቅርህ
ዘላለም ህያው አይበርድም
ዘላለም ህያው አያልቅም {x2}
ማለዳ ማለዳ
ነው ምህረትህ አዲስ {x4}
ጎን ሲቀድ ማለዳ ወፎቹ ሲያፋጩ
ህይወት ባገኝ ብዬ እደፋለሁ ፊቱ
አቤት የኔ ጌታ ማለዳ ምህረቱ
ተስፋዬንም አድሶ አቁሞኛል ቤቱ {x2}
ከፊትህ ያልጠፋነው ከብዙ ምህረትህ
ከህይወት የሚባለው አግኝቶናል እጅህ
በደምህ አንፅተህ ፀጋን ሞልተኽናል
በዝለት እንዳንወድቅ ሀይልህ በዝቶልናል
አንጠብቀው ነገን ቀኑን አናውቀው
አንዘጋጅ ነገን ቀኑን አናውቀው
እንደ ሌባ እኮ ነው ድንገት ሚመጣው {x2}
ይመጣል ብለን ዘመርን ዘመርን
ይመጣል ተባልን ተሰበክን
ድንገት ቢመጣ የት ነው ስፍራችን
አፅድተነው የሁን ጋዳ ቤታችን
መምጣትህን ዘንግተን በኃጥያት ተዘፍቀን
ዘይታችን አልቆ በጨለማ ሆነን
ነቅድስና መኖር ሲገባን
አንቀላፍተናል መምጫህን ረስተን
ኢየሱስ ይመጣል ታጅቦ በመልአክት
ልጆቹን ሊወስደን ወደ እርሱ ዘንድ
እንሄዳለን እኛም በአንድነት
እናየወለን ጌታችንን በእውነት
እነሆ በቶሎ እመጣለሁ
ለእያንዳንዱ እንደ ስራው እከፍለዋለሁ
አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኃለኛ
መጀመሪያውና መጨለሻው እኔ ነኝ
በአለም ዙሪያ ለሰው ሁሉ
ምክንያት አለው ለመኖሩ
ለህልዉናው ምንጭ የሆነ
አንድ የመኖር ተስፋ አለው
ለኔስ በራልኝ ሚስጥሩ
መዳን በእየሱስ መሆኑ
ኦሆሆ አንተን አገኘው
ኦሆሆ የዘላለም ሕይወቴን
ኦሆሆ ብርሀን በራልኝ
ኦሆሆ በመድሐኒቴ {2x}
ክርስቶስ እየሱስ በከፈለው ዋጋ
መዳን ሆኖልኛል{2x}
የሐጢያት ባርነት ኩነኔ ውድቀት
ሞትና መውጊያው ተሽሩአል
የሕይወት መዓዛ በላዬ ሆኑአል
አዲስ ፍጥረት ነኝ አሮጌው አልፉአል
ኦሆሆ አንተን አገኘው
ኦሆሆ የዘላለም ሕይወቴን
ኦሆሆ ብርሀን በራልኝ
ኦሆሆ በመድሐኒቴ {2x}
ሌላ አልተመኘሁም
በዓለም አልባዘንኩም
እንደ እየሱስ ያለ
አንድ አላገኘሁም
መዳኔ ነህ{3×} መዳኔ
ሕይወቴ ነህ{3×} ሕይወቴ
ደስታዬ ነህ{3×} ደስታዬ
በወደደን ጌታ በእየሱስ
ድነናል ከጥፋት ከሐጢያት ባርነት
ኦሆ ኦሆ መዳን ለኛ
ኦሆ ኦሆ ሆኖልናል
ኦሆ ኦሆ ቤዛችን እየሱስ
ኦሆ ኦሆ ሞታችንን ሞቷል
አንዴ ገብቶልናል ሊቀ ካኽናችን
ሊታይልን ወዶ ቅድስተ ቅዱሳን
እዉነት እና ምሕረት እዚያ ተገናኙ
ፅድቁም ሰላሙም ሞት እንዳያገኘን ተስማሙ
ኦሆ ኦሆ የዉርስ ሐጢያት በደል
ኦሆ ኦሆ እንዳይከተለን
ኦሆ ኦሆ በስራው በማመን
ኦሆ ኦሆ ዳግም ተወልደናል
ከመፈጠር ይልቅ ከእርሱ ተወልደናል
ከመላእክት እንኳን ጌታን ቀርበነዋል
ሰማይ ተከፈተ በክርስቶስ ስራ
መተያየት ቀርቷል ከመጋረጃው በስተጀርባ
ክበር እንበል በምስጋና
ጌታ እየሱስ ነህ ገናና
ንገስ እንበል በእልልታ
ይሁንል ከበሬታ
አብ አባታችን ወደ አዘጋጀልን
ቅዱሳን ሁላችን እንሄዳለን
እንሄዳለን{3×} ዘለአለም ልንኖር
የታረደውን በግ {2×}
ፊት ለፊት ልናየው {2×}
ልንኖር ከርሱ ጋር በደስታ በደስታ በሀሴት
ከመለአክቱ ልናመልክ በአንድነት
ምድራዊ የሚሆን ጊዜያዊ ስፍራችን
ልንተካው በአዲስ
አይን ባላየው
ጆሮ ባልሰማው
በእጅ ባልተሰራው
ጌታ ባዘጋጀው
እንሄዳለን{3×} ዘለአለም ልንኖር
አላቀርብም በዘመኔ እንከን ያለው መስዕዋት
የማይሆን ማይገባ ክብርህን ማይመጥን {2×}
ጌታ እስከ ሆንክ አምላኬ እስከ ሆንክ
መፈራት ለአንተ ይሁን
ጌታ እስከ ሆንክ አምላኬ እስከ ሆንክ
መከበር ለአንተ ይሁን
ክበር{×3} ጌታ እየሱስ
ንገስ(×3} ጌታ እየሱስ
ላንተ ኃያል ጌታ ስምህ ለተፈራ
ታላቅም ለሆንከው በምድርም በሰማይ
የምታሸተው ያማረ በአንተ ፊት
ይሁን አምልኮ በዜማ በሕይወት
ክበር{×3} ጌታ እየሱስ
ንገስ{×3} ጌታ እየሱስ
ንፁህ የሆነ አንተ ምትከብርበት
ይድረስ አምልኮ ነውር የሌለበት
ቅዱስ ሆነህ ተፈርተህ ላለኸው
ለአምላክነትህ ሚገባህ ይኼ ነው
ክበር{×3} ጌታ እየሱስ
ንገስ{×3} ጌታ እየሱስ
ምስጋና ምስጋና ዝማሬ ዝማሬ
ምስጋና በማደሪያ ላይ ላለኸው
ዝማሬ ቅዱስ አምላክ ለሆንከው {2×}
ለዘመንህ ጅማሬ የለው ፍፃሜ መጨረሻ
ለጌትነት እኩያ የለው ሚሆንህ ሐምሳያ
ዘላለማዊ ነህ አመታቶችህ አያልቁብህ
ሰማይና ምድር ሳትፋጥር ምስጋና የበቃህ
አመጣለሁ ዛሬም ምስጋናዬን ከልቤ
በመንፈስ ማደሪያህን ከብቤው
ውዳሴዬ ዙፋንህን ያውደው
ቅዱሱን ስምህን ያክብረው
ምስጋና በማደሪያህ ላይ ላለኸው
ዝማሬ ቅዱስ አምላክ ለሆንከው {2×}
አንተን አይቶ ክብርህን አይቶ
ማያመልክ ከየት ተገኝቶ {4×}
ኬስ ሞአቴ ኪ ሎምብ ሞአቴ
ኦቶሶቤ ሀንኦን ሄአቴ {4×}
ሰማያት ክብሩን ሚያወሩለት
ፍጥረታት የሚሰግዱለት
እግዚአብሔር ትልቅ ነው እኛም አናውቀውም
ክብርንና ግርማን የለበስህ
ብርሀንን እንደ ልብስ የተጎናፀፈው
ሰማያት የአንተን ፅድቅ ያወራሉ
ፍጥረታትም ሁሉ ክብርህን ያውጃሉ
ፊትህ እንደ ፀሀይ ያበራል
የፊትህ ሞገስ ማን አይቶ ይቆማል
ምድር እና ሞላዋ የእጆች ስራዎች ናቸው
በገና ማሲንቆም ተነሱ
እለት ተእለት ታላቅነቱን አወድሱ
እኔም ማልጄ እነሳለሁ
ታላቅነቱን ለፍጥረታት ዘምራለሁ
ሀሌሉያ ቅዱስ ስምህን እንባርክሀለን
የሕይወቴ ማምሻ ቀርቦ
መኖር ትርጉም አልባ ሆኖ
ነፍሴ ባክና ከመከራ
በሰቆቃ ድምፅ ስትጣራ
የጩኸቴን ቃል ሰማህ
እውነት ሕይወት መንገድ ሆንህ
ከዘላለም ጥፋት ዳንኩኝ
የመንግስትህ ወራሽ ሆንኩኝ
አንተ ለኔ ያደረከው እጅጉን ብዙ ነው
ቅኔ ቋንቋ ቃላቴም አይችልም ሊገልፀው
አ አኻ ኻኻኻ በደሙ ገዛኝ
አ አኻ ኻኻኻ አፀደቀኝ
አ አኻ ኻኻኻ ለነፍሴ ቤዛ
አ አኻ ኻኻኻ ምክንያት ሆነኝ
አመልክአለው{4×}
ዛሬ እንኳ እያለ በሕይወቴ ድክመት
የስንፍናን ወራት ያለማመን ብዛት
ለፈቃዴ ትተህ አልፈኸኝ አልሄድክም
ፀጋህን አይቻለው ሲሆነኝ አቅም
አንተ ለኔ ያደረከው እጅጉን ብዙ ነው
ቅኔ ቋንቋ ቃላቴም አይችልም ሊገልፀው
የማያልቅ ነው ምህረቱ
ሁል ጊዜ አዲስ ነው ታማኝነቱ
ማልጄ ተነሳሁ ሁ ሁ ሁ
ፍቅርህን አስቤ ሁ ሁ ሁ
አምላኬ አምላኬ ሁ ሁ ሁ
ወደ አንተ {x3} ገሰገስኩ
ዋላ ወደ ውሀ ምንጭ ሁ ሁ ሁ
እንደ ሚናፍቅ ሁ ሁ ሁ
አቤቱ አቤቱ ሁ ሁ ሁ
አንተን {x3} ተጠማሁ
አምላኬ አምላኬ {x3}
ወደ አንተ እገሰግሳለሁ
ሚታይ በሌለበት በደረቅ በረሀ
እንጨትም ውሃም በሌለበት ስፍራ
ነፍሴ ግን ጥማታ አንድ ነገር ነው
ሀይልህን ክብርህን ታይ ዘንድ ነው
እየሱስ ክርስቶስ የአለም መድኃኒት
ለሰው ልጅ መዳን ተጋ ቀን ከለሊት
መስቀል ተሸክሞ በጎልጎታ ሞቶ
እኔን አንተን አንቺን ነፃ ሊያደርግ ወዶ {x2}
አዳነን {x3} ራሱን ሰዋልን
አዳነን {x3} ቤዛ ሆነልን
ከሰማያት ወርዶ እራሱን አዋርዶ
ያለ ኃጢያት ሀጢያተኛ ሆኖ
ፍቅር አስገድዶት ታላቁን መከራ
ተወጣ ፃድቁ ሞታችንን ከክፉ
አዳነን {x3} ራሱን ሰዋልን
አዳነን {x3} ቤዛ ሆነልን
ከሰማይ ሰማያት ስለኛ ወረደ
የሰው ልጅን ሀጢያት በደሙ አስወገደ
መራራውን ፅቃ እርሱ ጠጥቶታል
በእየሱስ ቤዛነት መዳን ሆኖልናል
ወረደ ወረደ ንጉስ ተዋረደ
ያለ ሀጢያቱ ለኛ ሲል ወረደ
እኛ እንድንኖር እርሱ ሞቶልናል
የእግዚአብሄር ልጅ እየሱስ ነፃ አውጥቶናል
አምጡ ምስጋና ለታረደው በግ
ክብር ይሁንለት
ሞትን ድል ነስቶ በአብ ቀኝ ላለው
ክብር ይሁንለት
በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ
በድንግል ማሪያም ማህፀን አድሮ
የአለምን ሐጢያት ሊያስወግድ
ቤዛ ሆኖ መጣ ለአለም
አዳኝ•••••
በማሲንቆ እናመስግነው
በበገና እናመስግነው
በከበሮ እናመስግነው
በአዲስ ዜማ እናመስግነው
አዳኝ•••••
በቀራኒዮ ላይ ተሰቅሎ
ለሰው ልጆች ሁሉ ዋጋ አከፍሎ
ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና
መቃብር ፈንቅሎ ተነቷል ጌታ
እንዴት ያለ ምንጭ ነው የፈለቀልኝ
የዘላለም ጥሜንም የቆረጠልኝ
ከእየሱስ ሚፈልቀዉ የዘላለም ሕይወት
ደረቁን ሚያለመልም እንከን የሌለበት
አቤት እንዴት እንዴት ግሩም ነው
ለተጠማው የሕይወት ምንጭ ነው {x2}
ተነሺ ማለዳ ነፍሴን ለማመስገን
እንዴት ያስችልሻል የረገልሽ ነገር
ከጨለማ አውጥቶ ብርሀን ያበራልሽ
ቀንበርሽን ሰብሮ ነፃ ያወጣሽ
ተሽሮልሽ የሞት አዋጅ በእርሱ
ታወጀልሽ አርነት በእየሱስ
እርሱን የተከተለ ከልቡ ተማምኖ
ፍፃሜውም አማረ በጥላው ስር ሆኖ
በሆነለት ቤዛነት በእርሱ ያረፈ
ከሀጥያት ጥፋት ባርነት እርሱ አመለጠ
በቀራኒዮ ላይ ተሰቅሎ
ለሰው ልጆች ሁሉ ዋጋ አከፍሎ
ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና
መቃብር ፈንቅሎ ተነቷል ጌታ
አቤት እንዴት እንዴት ታደለ
በማዳን ሀይሉ በርሱ ያመነ {x2}
ይፈልቃል ምስጋና ሁሌ ከአንደበቴ
በአሰላሰልኩ ጊዜ መዳኔን በአባቴ
ቅኔን እቀኛለሁ ለስሙ ምስጋና
ባወድሰው አልቀር ጠዋትና ማታ
ተመስገንልኝ ከፍ በልልኝ
መዳኔ በአንተ ተፈፀመልኝ {x2}
ጌትነትህን ማውራት አቅቶኝ
ተገርሜ ጌታ ነህ አልኩኝ
ምህረትህን ማውራት አቅቶኝ
ተማርኬ መሐሪ ነህ አልኩኝ
ትልቅ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
ጌታ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
በሰማይ ሰማያት የከበርህ
የምድር ፍጥረታት ሁሉም ሚሰግዱልህ
ከጥንት የነበርህ ዛሬም ደግሞ ያለህ
በዙፋንህ ገነህ ዘላለም ትኖራለህ
ትልቅ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
ጌታ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
ብዙ ኃያላን በሞት ሲሻሩ
አንድም እንኳ በምድር ሳይቀሩ
አንተ ግን ያው አንተ ነህ አትለዋወጥም
በዘመናት መሀል እኩያ የለህም
ትልቅ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
ጌታ ነህ{3×} እኛም አናውቅህ
በአሰራርህ ተማርከናል
በምስጋና ልናመልክህ ወደናል {4×}
ልጆች ስንባል ባርነት ሲሻር
ሐጢያት ኩነኔ በፅድቅ ሲለወጥ ስናይ
ተሰብሮልን የሐጢያት ቀንበር
ነፃ ወጣን እየሱስ ወዶን
ምን ውብ ታሪክ አለን ስለእኛ ምናወራው
ፅድቃችን የሆነው የመርገም ጨርቅ ነው
ታሪካችን {3×} የተሰራልን በመስቀል
በሐጢያታችን ሙታን ሆነን ሳለን
የሚያስወድድ አንዳች ነገር የለን
የአለም ጠቢባኖች እያሉ
በእውቀት ዝና የተሻሉ
ወደኛ ደካሞች መጣህ
ካለንበት ማቅ ልታወጣን
ከስራችን ሳይሆን በፅድቅ ያገኘነው
የእየሱስ ልጅ መሆን እጅግ መታደል ነው
ፈፅሞ ሊተወን በማይቻል ፍቅሩ
ላይጠላን ወዶናል ይክበርልን ስሙ
ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ያለህ
ፍጥረታትን በሙሉ በስልጣን ታዛለህ
ይሁን ብቻ በሚለው ቃል ሁሉ የሆነልህ
የሰውንም ልጅ በኃምሳል ለክብርህ ፈጠርህ
ሰማያት ክብርህን ይናገራሉ
የሰማይ ጠፋር ስራህን ስራህን ያወራሉ
ቀንም ለቀን ሌትም ለሌት እዉቀትን ይገልጣል
ድምፃቸው እስከ ምድር ዳርቻ ይወጣል
እግዚአብሔር {4×} ክቡር ነህ {4×}
እውቀትህ ረቂቅ
ስራህ ሁሌም ድንቅ
ባማረ መዝሙር
ፍጥረት ይበልህ ክቡር
ክቡር ነህ {4×}
ድንቅ ነህ {4×} ሚመስልህ የለህ
የንጋት ከዋክብት በዘመሩ ጊዜ
መላእክት በአንድነት እልል ባሉ ጊዜ
የምድር መሰረት ማዕዘንኣ ቆመ
ይሁን ያልከው ሁሉ ቃልህን ታዘዘ
ከአማልክት መኃል እጅግ ባለግርማህ
ቅዱስነትህ ለፍጥረት ይሰማ
ዘመንህ የሌለው መነሻ መድረሻ
ዘለአለም ነዋሪ ጌታ አንተ ብቻ
የሽሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ
በደመናት ላይ ለታለቅነትህ {2×}
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለ {2x}
በእጆችህ ስራ በመገረም ተሞልተን
በምስጋና ማደሪያህ መጣን
በጌትነትህ እጅጉን ተደንቀን
በምስጋና ማደሪያህ መጣን
እልፍ አዕላፍት መላዕክት የሚሰግዱልህ
ሁሉን በስልጣንህ ቃል ገዝተህ የያዝህ
ይሁን በሚል ቃል ብቻ ሁሉን የፈጠርህ
የሰማይ የምድር ገዢ አንተ ነህ
ስለዚህ ጠዋት ማታ ክብርህን አይቼ
አመልክሀለሁ መቅደስህ ገብቼ
ስለሚገባህና
ስለተገባህ {x4}
ለከበርከው ለነገስከው
ተሰጥቼ አመልክሃለሁ
በዙፋን ላይ ለምትኖር ለማትቀየር
ጣፋጭ ዜማዬ ይኼው እ/ግር ክበር
ከብዙ አማልክት በሙሉ ለይቼ
አንተን አከብራለሁ እራሴን ቀድሼ
ስለሚገባህና ስለተገባህ
ምስጋና አምልኮ ውዳሴ ዝማሬ
ላቅርብልህ ላንተ ለሆንከው አምላኬ {x4}

online
Hi, I am Lidiya, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

online
Hi, I am Wenda, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

online
Hi, I am Wadola, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

online
Hi, I am Sara, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

online
Hi, I am Aman, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

online
Hi, I am Kali, and I am the leader of this choir. If you need to contact me, use my phone number or write your message here.

Developer
Hi, I am Kebron Ashenafi, How are you?

online

online

online

online

online

online

KicTov Developer


























